Tribute by Emahoy Aster, Sister
- Maro Haile
- Aug 3, 2021
- 1 min read
የሐዘን እንጉርጉሮ
ናፍቀኸኝ ጓጉቼ ላይህ በሕይወት
አንድ ሁለት ቃል እንድንጫወት
ተነስቼ ነበር ወገቤን ታጥቄ
አልከበደኝ ነበር ካገርህ መራቄ
አልታደልኩምና ቀረሁ ተሳቅቄ
መምጣቱንስ መጣሁ ግን ላላገኝህ
ሆዴ አልቻለምና መስሎኝ የማይህ
ከተውከን በኋላ ዝምታን መርጠህ
ልንገርህ ወንድሜ ከሆዴም አትወጣ
አይሀለው ብየ ብመኝም ብመጣ
ሳጥን ላይ መጮህ ሆነብኝ የኔ ዕጣ
እኔ ልተካልህ አስቤ ነበረ
እግዜር አልፈቀደም አልተቻለም ቀረ
መመለስ አይበለው ልቤ ቀርቷል እዛ
ወንድሜን አይቼው ተኝቶ እንደዋዛ
ምክርህና ፍቅርህ በሀሳቤ ተቀብሮ
መለየቴን ማመን አቃተኝ ዘንድሮ
አልቆጣጥረውም ውለታህስ ይቅር
አለሁሽ ማለትህ ለኔ በቂ ነበር
ወንድሜ የለህም ከንግዲህ አልኮራም
ይኸን ተናገረ ይኸን አደረገ ማለትን አልሰማም
ቃልህን ሙላልን እንገናኝ ናዝሬት
የናት የአባትህን ቤት መጥተህ ለመጎብኘት
እንደተመኘኸው ኢትዮጵያን ለማየት
እኛም አንሳቀቅ አንቅር በናፍቆት
ዓለም ፀሐይ መስሎ ይታየን ነበረ
እውነት ካንተ ጋራ ሞተ ተቀበረ ?
እህትህ እማሆይ አስቴር አስፋው
ከአዲስ አበባ
ኢትዮጵያ




Comments