top of page

40-Day Remembrance Remarks by Dr Melaku

ከ1993 እስከ 2017 የማሕበረ ግዩራን ዘር ኢትዮጵያ በሌላ ስሙ SEED Society of Ethiopians Established in Diaspora ሊቀመንበር ሆኜ ሰርቼአለሁ:: ድርጅቱንም የመሰረትንው በርከት ካሉ ጎደኞቼና ከቤተስቦቻቸው ጋር ነበር:: አንዱ መስራች ቤተ ሰብ በመሐከላችን አሁን እዚህ ከኛ ጋር ይገኞአሉ::


በ1993ድርጅቱ ለመጀመሪያ በውጭ አገር የምንኖር ኢትዮጵያውያን በስደተኞች ስም በደፈናው እንገለጽ ነበር:: ድርጅታችን ይህ ቃል ጠባብ በመሆኑ በተሻለ መንገድ እንድንታወቅ Ethiopian Diaspora የሚለውን ቃል በይፋ አስተዋወቀ:: ነገርግን በአማርኞ ተተርጉሞ ፍችው እንዲታወቅ በ1994 በአዲስ አበባ በሚገኙ ጋዜጦች እንዲተረጎምልን የውድድር ማስታወቂያ አወጣን:: ተቀባይነት ያለው ጥሩ ትርጉም ለአቀረበ $500 ድርጅቱ አንደሚከፍል አስታወቀ:: ከዘጠኙም ዞን ተወዳዳሪዎች ትርጉማቸውን ላኩ::


ፕሮፌሰር ጌታቸውና ዶር ሐይሉ ፉላስ አርኪ ብለው ያሰቡትን ትርጉም እንዲነግሩን የተሰበስቡትን ድብድቤውች ስብስብን ላክንላቸው:: ሁለቱም ምሑራን ያለምንም ክፍያ በተለይም ፕሮፌሰር ጌታቸው ጌዜያቸውን ወስደው ግዕዝንም መርምረው ዛሬ የምንጠራበትን ማህበረ ግዩራን ዘር ኢትዮጵያ የሚለውን ስማችንን አወጡልን:: ለዚህም ውለታቸው እግዚአብሔር ይክፈላቸው::


ዛሬ ማህበረ ግዪራን ዘር ኢትዮጵያ ከአገር ውጭ ካሉት አንጋፋ ከሚባሉት ድርጅቶች አንዱ ነው:: በየጊዜው በስራችን አንዳንድ ጉዳዮች ሲገጥሙን ምክራቸውን ይለግሱን እንደነበር አስታውሳአለሁ:: ሰው የስራው በጎ ስራ እንዲታወቅ ማድረግ በሕይወት እያለ መሆኑን ዘወትር ያስረዱን ነበር:: ይህም ምክር ለኛ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም አዲስ መጤ ድርጅትች የአበበ ቢቂላ ፋውንደሽን የጣይቱ ማዕከል እንዲሁም አገር በቅል በአገራችን ኢትዮጵያ የሚገኙ ሁሉ ድርጅትች ሰው በሕይወት እያለ መክብር አለብት ይሚለውን መምሪያ በመከተል ብዙ እንቅስቅሴ እያደረጉ ነው::


በ1996 ሶስተኛው የማህበረ ግዪራን ዘር ኢትዮጵያ ተሸላሚ በነበሩ ጊዜ የተናገሩት ንግግር ትዝ ይለኛአል:: የደርግ ወታደር በጥይት አቁስሏቸው ለሕክምና አበበ ቢቂላ የታከመበት ሆስፒታል ወደ ለንደን ተወስደው ነበር:: በ1973 አበበ ቢቅላን ያከመው ዶክተር ነበር ያከማቸው:: ሻምበል አበበም ፕሮፌስር ጌታቸውም ከወገባቸው በታች ሽባ ሆነው ነበር ሖስፒታሉን ለቀው ወደ ሐገራቸው የተመለሱት:: ከሐኪማቸው ጋር ሰለ ሻምበል አበበ አልፈው አልፈው ይወያዩ እንደንበር በSEED ስነስርዓት የተናገሩትን አስታውሳአለሁ:: ዶክተራቸው ሻምበል አበበ በሖስፒታሉ በቆየበት ጊዜ ብዙ እግዚአብሔር ይማርህ የሚሉ ካርዶች ከዓለም ይጎርፍለት ነበር ብሎ እንደነገራቸው ለታደመው ሰው ሁሉ መንገራቸውን አስታውሳለሁ::


እርግጥ ሻምበል አበበ የመጀመሪያው ጥቁር አፍሪካዊ የኦሎፒክ አሸናፊ በመሆኑ የጠቅላላው አፍሪካ አሕጉር ና በሌላውም ዓለም ሕዝብ ዘንድ ስለሚያውቀው ከብዙ ቦታ ካርዶቹ መጥተውለት ይሆናአል:: ፕሮፌሰር ጊታቸው በዚያን ዕለት እንደመልእክት ያሰለፉልን ነገር ቢኖር ሳንሞት በሕይወት እያለን ማመስገን መማርን ነው:: ሲድ የጀመረው ባሕል ግሩም ስለሆነ መበራታት እንዳለበት መጠቆማቸው ነው:: የኛ ባሕል ሰውን ከሞተ በሗላ የሚይወድስ በመሆኑ ሁለቱንም ማድረጉ ጠቃሚ ነው ማለታቸው ነው::


ስለ ፕሮፌሰር ጌታቸው ምሁራዊ ስራዎች ስለ ስባዓዊ መብቶች ስለ ዲሞራሲ በኢትዮጵያ ለአደረጏቸው ትግሎችና ልፋቶች በሌላ መድረክ ስለተገለጹ በኔ ንግግር ላይ አልተካተቱም:: ለማሕበረ ግዩራን ዘር ኢትዮጵያ ለእደረጉት አተዋጽኦ አምላካችን የሚገባቸውን መንግሥተ ስማያት ያጎናጽፍልን:: አሜን!!

6 views0 comments

Comments


bottom of page