Poem by Zufan Lemma
- Maro Haile
- Aug 3, 2021
- 1 min read

የሃዘን እንጉርጉሮ
እንቧ ይላል በሬ አጣማጁን ሲያጣ
በቃኝ ብለህ ስትሄድ እንዴት አንጫጫ!
ታሪኳን መዝጋቢ ኢትዮጵያ ስታጣ
አንተን የመሰለ ዐዋቂ ጠበቃ
አጣች መከታዋን እምዬ ኢትዮጵያ።
አንጋፋው መምህር የብዕሩ ጀግና
የወጣቱን ትውልድ ተክተሃልና
አሻራህ ይኖራል እስከ ዓለም መጨረሻ
የኢትዮጵያዊነታችን ተምሳሌት መግለጫ።
እኛም ዘመዶችህ ያልጠገብንህ ገና
ይሻልሃል ብለን ስንጠብቅ በተስፋ
ሆነብን ሃዘንህ እንደ እሬት መራራ
ጉዞህን አሳመርክ ዳግመኛ ላትመጣ።
በል ደህና ሁንልን የሸንኮራው አርበኛ።
ሰላምታ አድርስልን ለአብዬ ሃይሌ ለሺመቤት ዲና
ጋሼ ጌታቸው ነፍሥህን በአጸደ ገነት ያኑርልን።
- ዙፋንሽ ወርቅ(ዙፋን) ለማ
Comments