top of page

Tribute by ዘካርያስ ጌታቸው እና ቤተሰበ

ለምን እንጮሃለን

አረ ለምን?

አረ ለምን ለዚህ ታላቅና ረቂቅ ሰው።

ከአምላክ የተሰጠንን ማንንነት ስላተለቀው

አረ ለምን

እናት አገርን የኛ ብቻ ሳትሆን የመላው ጥቁር

ስላስመሰለው

ቋንቋችንን እንዲከበር ፊደላችን እጅ እንዲነሳለት ስላደረገው

እንዴ ለምን ትጮሄአለሽ

ተተኪ የለሽ ሆነና? ብዕሩን ሌላው ስላልወረሰው?

እንዴ ለምንድን ነው ጩኽቱ

ስድስት አምላክ ሰቶት የልጅ ልጁን አስር ያየ

አረ ለምን

ባህረ ሃሳብን፣ ዘረያቆብን፣የነአባ እስጢፋኖስ፣

አረስንቱ፡ አስረክቦን

የአሃዱን ያቦጊዳን ያግእዝን አስከብሮ

ለትውልዱ አስረክቦ

ምሰሶዋን ኦርቶዶክስን ተራራው ላይ ቁጭ አድርጎ

አረ ለምን ይጮሃል

ከላይ ያለውም ይቆጣል

ኪነጥበብ ባህላቱን በልዩ መልክ ብሎ እንካችሁ

ፖለቲካን አገራዊና ህዝባዊ ካልሆነ ያልነካው

ምን በወጣው

ታዲያ ለምን እንጮሃለን

ለምን ትጮሃለህ እኮ ነው ያልከኝ?

አረ ወይግድ እጮሃለው። ለምን አልጩህ

ለምን አልጩህ ለአገሬ፣

ለምን አልጩህ ለዛ ህዝቤ

ለምን አልጩህ ለኦርቶዶክስ

ለምን አልጩህ ለዛች ፊደል

ለምን አልጩህ ለዛ ግእዝ


ርክክብ ለሌለበት ዘመን

የኋላውን አጥፍቶ የሱን መቀባት የሚፈልገውን

እያየሁ እንዴት አልጩህ

ምድር ሚዛኗ ተደፋ

ትልቁን ሰው አጣችና

አልተገዛን እጅ አልነሳን

ለዘመናት ግን ደረቅን

ማን ሊያረጥበው ይሄን ድርቀት፡

አረ አረ በማርያም በማን ብዕር

ለምን አልጩህ

አይተኪው በቃ አለን

አረ በቃኝጨረስኩ አለን

እማማ ኢትዮጵያ ምን እያልሽ ነው

አረ አንድ በይ

ሚስጥርሽን ቅኔሽን ማን ይፍታው

ብራናውን ማን ይግለጠው

እጮሃለው በጩኸቱ ግን አልወድቅም

ያገር ዋርካው ይላል መጮህ አቁም

ጊዜ አትታጥፋ ለኔ ሳይሆን ላገርህ ጩህ

ይልሃል ቁም እንደዘብ

አስረክቧል ታላቅ ጥበብ

ሰቶሃል የታሪክ ክምችት

ተጠቀመው ካወክበት

እሱ ዘና ብሏል ከጌታው ጋር

ፕሮፌሰሩ ያጌታቸው

ምን ቀረበት በዚች ምድር

ነፍስ ይማርልን

ለቤተሰቡ መፅናናትን ይስጥልን

ዘካርያስ ጌታቸው እና ቤተሰቡ

ሰኔ ፲ ፳፻፩፫ ዓ/

7 views0 comments

Comments


bottom of page