top of page

40-Day Remembrance Remarks by አልማዝ ዘውዴ ዶ/ር

ዶክተር ጌታቸውና ኢትዮፕያዊነትስለ ዶክተር ጌታቸው ጥቂት ትውስቶች

አልማዝ ዘውዴ/ዶር


ምንም እንኩዋን አዲስ አበባ እያለን በሩቁ የምንተዋወቅ በሆንም፤ እኔ ዶክተር ጌታቸዉን በቅርብ መተዋወቅ የጀመርኩት እንደ አዉሮፓውያን አቆጣጠር ወደ 1990 አካባቢ አሁን ባለንበት አገረ አሜሪካን ነው። እኔ ከምኖርበት ሚቺጋን እሱም ከሚኒሶታ ድረስ እየተጓዝን በ ዲትሮዮት፤ ዋሽንግተን ዲሲ ቦስቶን ስብስባዎች ላይ እንገናኝ ነበር። ስብሰባዎቹ ትልቅ በሆኑ ትንሽ እኩል አክብሮ በዊል ቸር ላይ ሆኖ እየተጓዘ አገልግሎቱን ይሰጥ ነበር። ብዙ ቦታዎች ላይ ዋና ተናጋሪው እሱ ነበር።


ከታሪክ ሊቅነቱና ከአስተሳሰቡ ሚዛናዊነት የተነሳ በየስብሰባው ንግግሩን በጉጉት የሚጠብቁ ጥቂት አልነበሩም። ሁላችንም ትክክለኛዋን ታሪካዊ ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ጉዳዮች ለትምህርትም ሆነ ለምክርም የምንመለከተው ወደ ዶክተር ጌታቸው ነበር።


በ1992 መጨረሻ ላይ እኔ ከሚቺጋን ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ከመጣሁ በሁዋላ የበለጠ መገናኘትና አብሮ መስራትም ጀመርን፡


የአብሮ መስራታችን መነሻ እንዲህ ነበር፡


በ1993 አንድ አስራ ሁለት የምንሆን ኢትዮጵያውያት ተሰባሰብንና ስለኢትዮጵያ አሳዛኝ ሁኔታ መወያየት ጀመርን።


በጊዜው ወያኔ ስልጣን ይዞ በማህበራዊ፤ በፖለቲካና በኢኮኖሚ መስኮች የሚሰራቸው ግልጽና ስዉር ግፎች ለኢትዮጵያና ለህዝቡዋ እጅግ አደገኛ መሆናቸው ታይቶን የምንጨነቅ ነበርን። ከብዙ ውይይቶች በሁዋላ እኛ ብቻችንን ምንም ነገር ለማድረግ አቅም ስለሌለን እስኪ ጥቂት ስመጥር ኢትዮጵያንን እናሰባስብና እንዲወያዩበት እናድርግ ብለን ተነሳን። ለሚሰበሰቡት ታዋቂዎችም የመወያያ ነጥቦችነና የመነሻና የአጭር ጊዜ የዕቅድ ሃሳቦችንና ስልቶችን በመሰለን ልክ አዘጋጀን።


ስለ ሃሳባችን በመጀመሪያ ካማካርናቸው ሶስት አንጋፋ ምሁራን ውስጥ ዶክተር ጌታቸው አንዱ ነበር። እነሱም ካዳመጡንና ብዙ ጠቃሚ ሃሳቦችን ካነሱ በሁዋላ በርከት ያሉ ሰዎች ተሰባስበው ዉይይት ቢካሄድ እንደሚበጅ መከሩን። በስብሰባው እንዲገኙ የሚታሰቡትን ሰዎች ስም እንድናሰባሰብና ፈቅደኝነታቸዉንም እንድንጠይቅ ከዚያም ስብሰባዉን እንድናዘጋጅ ተስማማን። ይህንን ካጠናቀቅን በሁዋላ ስብሰባው በ1993 አጋማሽ አካባቢ ብዙ ምሁራንና የሃገር ሽማግሌዎች በሲልቨር ስፕሪንግ ከተማ ተሰባስበው ከመከሩ በሁዋላ አንድ የሁሉንም ኢትዮጵያውያን ታጋይ ድርጅቶችና ጥረቶች በቅንጅት እንዲሰሩ የሚአግባባና በህዝብ ስም የሚመክር፤ ሲቻልም የሚአስተርባብር ድርጅት ለማቋቋም ስምምነት ተደረገ። የድርጅቱም ስም “የኢትዮጵያ አንድነት አስተባባሪ ኮሚቴ” ተብሎ እንዲጠራ ተወሰነ። ድርጅቱም በአፋጣኝ በህግ እንዲመዘገብ ተወሰነ።


በአመዘጋገብ ጉዳይ አኛ ሲቶቹ በሁዋላ ውይይት ስናደርግ ይህ ኮሚቴ ከጎኑ የሴቶችና የወጣቶች ኮሚተዎች ተቋቁመው በስራ በረዱት የተሻለ ዉጤት ሊገኝ ይችላል ብለን ስላሰብን አንድ ሰፋ ያለ አጀንዳ ይዞ ሊሰራ የሚችል ድርጅት በማቋቋም ሶስቱም ኮሚቴዎች ራሳቸዉን ችለው ግን በመተባበርና በመደጋገፍ እንዲሰሩ ለማድረግ የሚአስችል አደረጃጀት አዘጋጅተን ሰፊዉን ድርጅት አዋቀርነው። ይህ ድርጅትም “የኢትዮጵያ ትምህርትና ልማት ህብረት” ተብሎ በህግ እንዲመዘገብ ተወሰነ። የድርጅቱም ህጋዊ ምዝገባ በማሳቹስትስ ግዛት ተፈጸመ.።


የኢትዮጵያ አንድነት አስተባባሪ ኮሚቴም በታቀደለት መሰረት ለአመታት ብዙ ጠቃሚ ስራዎችህን ሲሰራ ቆየ።ብዙ እንቅፋቶችንም እየተቋቋም ኢትዮጵያና ሃዝቡዋ በነጻነት እንዲኖሩና ሕዝቡዋም በሁሉም ዘርፍ የማደግ እድሉ እንዲጎለብት፤ ሰባዊ መብቱ እንዲከበርና ኢትዮጵያም እንደሃገር እንድትቀጥል ኢትዮጵያዊ ነን የሚሉ ድርጅቶች ሁሉ በህብረት እንዲሰሩ ብዙ ትግሎችን ሲአደርግ ቆየ። ያ ወቅት የጸረ ኢትዮጵያ ሃይሎች አመለካከት እጅግ የተጠናከረበትና በመንግስት ደረጃም ሳይቀር የሚደረገው ስልታዊ ትግል “ኢትዮጵያ” የሚለዉን ስም፤ታሪካዊ ማንነትና ጂኦግራፊ የመሰረዝ፤ የማጣጣልና፤ የማጥላላት ዘመቻ ተጠናክረው የሚካሄዱበት ስለነበር ኢትዮጵያዊነት እንዳይጠፋ መታገልም አንዱ ዓላማ ነበር።


የሃገራችን ችግሮች በየጊዜው የበለጠ እየሰፉና እየተለዋወጡ ሲሄዱ የተለያዩ ስልቶችን በመቀየስና ከሌሎች ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ጋር በመተባበር፡ አዳዲስ ንቅናቄዎችም በመመስረት ዶክተር ጌታቸውና አጋሮቹ እስክ 2020 አጋማሽ ድረስ ያለማቋረጥ ጥረዋል።


ዶክተር ጌታቸውና ያልተለዩት የትግል ጓዶቹ ከጥቂት ተመሳሳይ ዓላማ ከነበሯቸው ቡድኖች ጋር በመሆን ያቋቋሟት የመጨረሻ ድርጅት “ኢትዮጵያዊነት፡ የዜጎች መብት ማስከበሪያ ድርጅት” የሚባለው ከዘጠኝ አመት በፊት የተቋቋመው ድርጅት ነው።


በረጅሙ ኢትዮጵያን ለማገልገል ባደረግነው ጉዞ ዶክተር ጌታቸው ሁልጊዜም በዕውቀቱ፤ በገንዘቡ፤ በጊዜው ለመርዳት ፊት ቀደም ሆኖ ኖሮአል። የኢትዮጵያን ታሪካዊ ዕውነታዎች ለመረዳትም ሆነ ሆን ተብሎ የተጣመሙ ትርክቶችን ለመጋፈጥ ሁሌ ሃሳብ የምንጠይቀው እሱን ነበር። ለአንዳንዶቻችን ኢትዮጵያን በተመለከተ ኢንስይክሎጲዲያችንና ቃላት መፍቻችን እሱ ነበር። እሱም ሳይሰለች ጥያቂአችንን ሁሉ በደስታ ይመልስ ያስተምረንም ነበር። ለበጎ ብለዉም ቢሆን ታሪክ እጅግ አዛብተው የሚአቀርቡ ሰውችን ምሁራዊ ባህሪን በተላበሰ መልክ ያርም ነበር። ለምን ታረምን የሚሉ ሰዎች የስድብ ናዳ ሲአወርዱበት እሱ አንድም ቀን የቁጣ ወይም የዘለፋ ቃል አይሰነዝርም ነበር።ይህን ሁሉ የማነሳው በየአጋጣሚው ከሱ የተማርኩአቸውን ብዙ ጠቃሚ ነገሮች ለማስታወስ ነው።


ወንድማችን ዶክተር ጌታችሀው ወደ እማይቀርበት የክርስቲያኖች የዘለላም ቤት የሄደ ቢሆንም መልካም ትዝታው ሁሌም አብሮን ይኖራል። እግዚአብሄር ነፍሱን ከደጋጎቹና ከብጿኑ ማሃከል ያኑርልን።17 views0 comments

Comments


bottom of page