ጋሽ ጌታቸው;
ተምሮ አስተማሪ
ጥበብን መካሪ
እውነትን መስካሪ
የሀቅ ልክ ሚዛን የፍትህ ርዕትህ ተሟጋች ታታሪ
አንደበተ ርቱዕ የብዕር አርበኛ
ጉንቱ ባለቅኔ የሥነመለኮት ጥልቅ ሚስጥረኛ
ስለ ድንቅ ውለታህ ላገር ለከፈልከው ለትውልድ ትሩፋት ለታሪክ ለተውከው
ልክተብ በብዕሬ ልመስክር በቃሌ
ከምሁራን ጎራ ከጠበብት ሸንጎ
ማን ይስተካከላል ከጌታቸው ኀይሌ::
ሥዪም ወርቅነህ
ብሌን ሚኒሶታ
Getatchew Haile
Getatchew Haile
1932 - 2021
Comments