top of page

የሀዘን መግለጫ

Originally published on the front page of https://www.ethiopiawin.net/.

ሰኔ 4 ቀን 2013 ዓ/ም

በታላቁ ምሁር በፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ህልፈተ ሕይወት የተስማንን ጥልቅ ሀዘን በራሳችንና በመላው የኢትዮጵያዊነት ድርጅት አባሎቻችን ስም እንገልፃለን። ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው ሁሉ መፅናናትን እንመኛለን።

ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ድርጅታችንን ከመሠረቱት ጥቂት ግለሰቦች መሀከል አንደኛውና ዋነኛው ሲሆኑ፤ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ንቁ ተሳታፊና ድርጅታችንን በሀሳብ፤ በገንዘብና በፅሁፍ ሲረዱን ከቆዩት መካከል ናቸው። ።

ፕሮፌሰር ጌታቸው በኢትዮጵያ ታሪካና ሥነ ጽሁፍ ዕውቀት፡ ችሎታቸውና ተመራማሪነታቸው በሀገራችን ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፉ ሕብረተሰብ ከፍትኛ ቃዋቂነትን ያተረፉ ታላቅ ሰው ነበሩ። ለዚህም ከተለያዩ ድርጅቶችና መንግሥታት የበጎ ሥራዎች ሽልማትና የዕውቅና ማዕረጎችን ከከፍተኛ ክብር ጋር አግኝተዋል። እ ኤ አ በ1988 ከአሜሪካን መንግሥት የተበረከተላቸው የማካርተር የበሳል አእምሮና ምጡቅ ተመራማሪ ሽልማት በመስኩ የመጀመሪያው ተሸላሚ አድርጎ አቸዋል።

ፕሮፌሰር ጌታቸው ደከመኝ ስለቸኝ ሳይሉ በዘመናቸው በተለይም ከኢትዮጵያ ታሪክ ቅርስ፣ ባህልና ሃይማኖት ጋር የተያያዙ በርካታ መፃህፍት ፣ የምርምርና የጥናት ፅሁፎችን አበርክተዋል። አብዛኞቹም በአማዞን ድረገፅ በኩል የሚታደሉ ናቸው።

ሀገራችን ዛሬ አንጋፋ ልጅዋን አጥታለች። ለሁላችንም እግዚአብሔር መፅናናቱን እንዲስጠን እየጠየቅን፤ የእሳቸውንም ነፍስ በአፀደ ገነት እንዲያኖርልን እንለምናለን።

ኢትዮጵያዊነት፤ የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባኤ

የሥራ አመራር ቦርድ
ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ

21 views0 comments

Comments


bottom of page